ስለ አርኬ ዲጂታል

የአርኬ ምንነት (The Essence)

አርኬ ዲጂታል እውቀትን ከስነ-ምግባር ጋር አጣምሮ የያዘ፣ የአገር በቀል እውቀትና የአካዳሚክ የላቀ ብቃትን ለቀጣዩ ትውልድ ለማድረስ የተቋቋመ የትምህርት መድረክ ነው።

ዋና እምነታችን (Core Belief)

እውቀት ያለ ስነ-ምግባር ፍሬ ቢስ ነው፤ ስነ-ምግባር ደግሞ ያለ እውቀት የተሟላ አይሆንም። እውነተኛ ስኬት የሚገኘው ሁለቱን ስናዋህድ ነው።

ራዕይ 2035 (Vision 2035)

በ2035 በምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም እውቀት አቅራቢ በመሆን፣ ከ1 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን በስነ-ምግባር የታነጹ መሪዎች ማድረግ።

ተልዕኳችን (Mission)

የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ብቁ እና ታማኝ መምህራንን ከተማሪዎች ጋር ማገናኘት እና የትምህርቱን ሂደት ግልጽ በሆነ መንገድ መምራት።

የየኔታ አስጠኚ (የመንፈሳዊ እና ባህላዊ ትምህርት)

ለልጆችዎ ባህላዊ እና መንፈሳዊ እሴቶችን፣ ግዕዝ፣ ዜማ እና ስነ-ምግባርን በብቁ የኔታዎች በቤቶት ያስተምሩ። አሁን በመስራት ላይ ይገኛል።

የፊደል አስጠኚ (የአካዳሚክ ድጋፍ)

የክፍል ትምህርትን የሚያግዝ፣ ሂሳብ፣ ሳይንስ እና ቋንቋዎችን ያካተተ ዘመናዊ አካዳሚክ አስጠኚ። በቅርብ ቀን የሚጀመር።