

መንፈሳዊና ባህላዊ የቤት ውስጥ ትምህርቶች
በቤተክርስቲያን የተመሰከረላቸውን ብቁ የኔታዎች ከተማሪዎች ጋር በማገናኘት፣ በቤቶት ሆነው ግዕዝ፣ ቅዳሴ፣ ዜማ እና ስነ-ምግባርን ያስተምሩ።
የየኔታ አስጠኚ የትምህርት ጥቅሎች
ፍላጎትዎን መርጠው ዛሬውኑ ይመዝገቡ። ክፍያው የአገልግሎት ክፍያ 100 ብርን ጨምሮ ጠቅላላ ወርሃዊ ዋጋ ነው።
መሠረተ-እምነት (Meserete Emnet)
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሠረተ እምነት፣ ጸሎትና ስነ-ምግባር ትምህርት
4,199ETB / ወር
የትምህርት ይዘቶች (Syllabus)
- መሠረተ ሐይማኖት፣ ታሪክ፣ ቅዱሳን መፃህፍት፣ ሥነ-ምግባር፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ክርስቲያናዊ ማንነት
- 5ቱ ዓዕማደ ሚስጢር፣ 7ቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን፣ ሐይማኖተ አበው፣ ትምህርተ ሐይማኖት፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ነገረ መለኮት፣ ነገረ ክርስቶስ፣ ነገረ ማርያም፣ እቅበተ እምነት
- የእምነት መሠረቶች – ጥልቅ የሆነ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ትምህርቶች
- ቅዱሳት መጻሕፍትና ታሪክ – የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ የቤተክርስቲያንና የሀገር ታሪክ
- የቅዳሴና የልዩ ልዩ የአምልኮ ሥርዓቶች ዝርዝር ጥናት
- የሥነ-ምግባርና የአኗኗር ሥርዓቶች – ክርስቲያናዊ የሥነ-ምግባር መመሪያዎች
- የመንፈሳዊ ልምምድና ጸሎት – ለዕለት ተዕለት መንፈሳዊ ሕይወት የሚረዱ ሥርዓቶች
ቋንቋና ዜማ (Quanquanna Zema)
የግዕዝ ቋንቋ፣ የፊደል ንባብ እና የመዝሙር/ዜማ መሰረታዊ ትምህርቶች
5,499ETB / ወር
የትምህርት ይዘቶች (Syllabus)
- የግዕዝ ፊደልና ንባብ – የፊደል አጻጻፍና አወራረድ ሥልጠና
- የግዕዝ ሰዋስው – መሠረታዊ የግሰ ሥርዓቶች
- የግዕዝ መዝገበ ቃላት – በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቃላትና አባባሎች
- መሠረታዊ የዜማ ትምህርት – የመዝሙር ዜማ መሠረቶች
- የሰንበት ትምህርት ቤት እና የማኅበረ ቅዱሳን መዝሙራትና ዝማሬዎች – ታዋቂ ዝማሬዎችን መዘመርና መለማመድ
- የቅዳሴ መሠረታዊ ዜማና ንባብ – ለጀማሪዎች የሚሆን ሥርዓታዊ ትምህርት
የድቁና ዝግጅት (Diquna Zegajat)
የድቁና መዓርግ ለማግኘት ለሚፈልጉ የቅዳሴና የዜማ ጥልቅ ትምህርት
5,999ETB / ወር
የትምህርት ይዘቶች (Syllabus)
- የቅዳሴ ዝግጅት – የቅዳሴውን ሥርዓትና አወራረድ በዝርዝር መማር
- የድቁና አጠቃላይ ትምህርቶች – የቤተክርስቲያን አስተዳደርና አገልግሎት
- የዜማና መዝሙር ክህሎት – ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚሆን ሥልጠና
- የመጀመሪያውና የሁለተኛው ዙር ቅዳሴ – የተሟላ ሥልጠና
- ውዳሴ ማርያም ንባብ እና ዜማ, መዝሙረ ዳዊት፣ በመልክአ ሕማማት፣ መልክአ ቁርባን፣ ቅዳሴ ትምህርት እና ሌሎች።
- የልዩ ልዩ የአምልኮ ሥርዓቶች – በድቁና አውድ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት
የሙሉ ትምህርቶች ጥቅል (All Courses Bundle)
ሁሉንም የመንፈሳዊ ትምህርት ክፍሎች ያካተተ ሁለንተናዊ ጥቅል
7,999ETB / ወር
የትምህርት ይዘቶች (Syllabus)
- ሁሉንም የመንፈሳዊ ትምህርቶች ክፍሎች – በሁለቱ ጥቅሎች ውስጥ ያሉትን በሙሉ
- የተጨማሪ እውቀት ክፍሎች – ስለ ቤተክርስቲያን፣ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍትና ስለ ሥነ-ምግባር ጥልቅ ትምህርቶች
- የቅዳሴና የድቁና ዝርዝር ሥልጠና – ለተሟላ ዝግጅት የሚረዱ ትምህርቶች
- የዜማና መዝሙር ክህሎት – ለሁለቱም ዘርፎች የሚሆን ሥልጠና
- የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ትምህርቶች – በሁለቱ ጥቅሎች ውስጥ የተሟላ ትምህርት
- ለዕለት ተዕለት መንፈሳዊ ሕይወት የሚረዱ ሥርዓቶችና ልምምዶች
የየኔታ መምህር ነዎት?
በክብር ሙያዎ ተማሪዎችን እያስተማሩ 85% ክፍያ በማግኘት ኑሮዎን ያሻሽሉ። ዛሬውኑ ይመዝገቡ።